1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃውያን ስደተኞች ሰቆቃ በሊቢያ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 3 2010

የሰው ልጆች ሁሉ ነፃ እና እኩል መብት ያላቸው ናቸው ይላል እአአ በ1948 ዓም የተፈረመው የተመድ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌ  ሰነድ የመጀመሪያው አንቀጽ። ይህ መሪ ቃል  ሰባኛ ዓመት ሊደፍን ጥቂት ጊዜ በቀሩት ባሁኑ ወቅት በሊቢያ ጥቁር አፍሪቃውያን እንደ ዕቃ ለባርነት ቀንበር መዳረጋቸው አሳዛኝ እና አሳፋሪ ክስተት ሆኖ ታይቷል።

https://p.dw.com/p/2pCkp
Libyen Lager für Flüchtlinge
ምስል picture-alliance/dpa/B. Schwinghammer

ስደት

ይኸው በሊቢያ የሚካሄደው የባርያ ንግድ በተለይ ካለፉት ጥቂት ጊዚያት ወዲህ የመገናኛ ብዙኃንን ትኩረት አግኝቷል። ባለፈው ሳምንት በኮት ዲቯር የአቢዦ ከተማ የተሰበሰቡት የአፍሪቃ እና የአውሮጳ መሪዎችም ይህንኑ በስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለውን ኢሰብዓዊ ድርጊት እና የመብት ጥሰት ለማብቃት ስምምነት መድረሳቸው ይታወሳል። በተለያዩ አስገዳጅ ሁኔታዎች ከሀገር ቀያቸው የተሰደዱ አፍሪቃውያን ከአስቸጋሪው የሰሀራ በረኃ ጉዞ በኋላ ፣ በሊቢያ የሕገ ወጥ ሰው አሸጋጋሪዎች የባርነት ቀንበር  ውስጥ ወድቀዋል፣ አሁን በፈረንሳይ ተገን የጠየቀ አንድ ኢትዮጵያዊ ስደተኛም ራሱ የሕገ ወጥ ሰዎች አሸጋጋሪዎች የባርነት ቀንበር ሰለባ እንደነበር ለዶይቸ ቬለ ገልጿል።

ሀይማኖት ጥሩነህ
አርያም ተክሌ