1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ማርሻል ፕላን እና ኢትዮጵያ

ዓርብ፣ ግንቦት 4 2009

በድሃና ሃብታም ሃገራት መካከል ያለዉን ልዩነት ለማጥበብ እንዲቻል አፍሪቃ ጋር ተቀራርቦ መሥራት ያለመ ዕቅድ ያዘለ የመነጋገሪያ ሰነድ ሰሞኑን በርሊን ላይ ቀርቦ መወያያ ሆኗል።

https://p.dw.com/p/2ctBc
Deutschland Brandenburger Tor Berlin
ምስል picture-alliance/Bildagentur-online/Schoening

Beri. Berlin (Marschallplan und die äthiopische Politik) - MP3-Stereo

 የጀርመን መንግሥት እና 20ዎቹ በእንዱስትሪ ያደጉት ሃገራት ለአፍሪቃ ችግር መፍትሄ ይሆናሉ ብለዉ ያቀረቡት ሃሳብ ዋና አላማዉ ለስደት ምክንያት ይሆናሉ ተብለዉ ለሚገመቱት ምላሽ ለማፈላለግ እንደሆነ ተገልጿል። መነጋገሪዉ ሰነድም በሁለት አበይት ጉዳዮች ላይ ያነጣጠረ መሆኑን የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል የላከል ዘገባ ያስረዳል። በኤኮኖሚ እድገት እና በመልካም አስተዳደር፤ እንዲሁም በሕግ የበላይነትም ላይ ያተኩራል። በርሊን የኮንራድ አደናወር የበጎ አድራጎት ድርጅት ባዘጋጀዉ በዚህ መድረክ ላይ የኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ