የአዲስ አበባ ጅቡቲ ባቡር መስመር
የኢትዮጵያን የኤኮኖሚ እድገት ያፋጥናል፣ ከጎረቤት ሃገራት ጋር ያላትንም ትስስር ያጠናክራል የተባለለት 656 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለዉ የአዲስ አበባ ጅቡቲ የባቡር መስመር ግንባታ ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ እንደቀጠለ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን
የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ የአዲስ አበባ ጅቡቲ ባቡር መስመር የፉሪ ለቡ ባቡር ጣቢያ እጎአ ህዳር 28፣ 2007 ዓም ተቋቋመ።
የባቡር መስመር
ከአዲስ አበባ እስከ ጅቡቲ ድረስ የተዘረጋው 656 ኪሎሜትር ርዝመት ያለው የባቡር መስመር ፕሮጀክት በኢትዮጵያ መንግሥት ነው የተገነባው። ይኸው በአራት ዓመት ውስጥ የተጠናቀቀው ፕሮጀክት 3,4 ቢልዮን የዩኤስ አሜሪካ ዶላር ፈጅቶዋል።
ዘመናይ ባቡር
ዘመናዮቹን ባቡሮች የሚያቀርቡት ፕሮጀክቱን የያዙት የቻይና የስራ ተቋራጮች ናቸው። ተጎታቾቹን ባቡሮች ደግሞ መጀመሪያ ላይ ከውጭ በማስገባት ወደፊት ኢትዮጵያ ራሷ ለማምረት የሚያስችላትን አቅም እያዳበረች ትገኛለች።
የባቡሩ ፍጥነት
መንገደኞች የሚያመላልሰው የባቡር ፍጥነት በሰዓት 120 ኪሎሜትር፣ ዕቃ የሚያጓጉዘው ደግሞ 90 ኪሎ ሜትር በሰዓት ነው። ባቡሩ በምሥራቅ አፍሪቃ በኤሌክትሪክ የሚሰራ የመጀመሪያው ሲሆን፣ ለእንቅስቃሴው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ይጠይቃል።
የባቡሩ ሰራተኞች
የባቡሩ መስመር ግንባታ እና ባቡሩን የማንቀሳቀሱ ስራ አሁን ሙሉ በሙሉ በቻይናውያን የሚከናወን ሲሆን፣ ወደፊት በኢትዮጵያውያን ለማንቀሳቀስ ጥረት ተጀምሮዋል። በሩስያ፣ በቻይና እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተካሂዷል። ከዚህ በተጨማሪ የስልጠና ትምህርት ሊሰጡ የሚችሉ 120 ኢትዮጵያውያን በቻይና ሰልጥነው ተመልሰዋል። አሁንም ከቻይናውያኑ ጋር በጋራ በመስራት ላይ ይገኛሉ።
የመንገደኞች ማመላለሻው ባቡር
የመንገደኞች ማመላለሻው ባቡር ምቾቱን የጠበቀ ሲሆን በአንድ ጊዜ ብዙ መንገደኞችን ማመላለስ ያስችላል።
የባቡሩ መስመር ምረቃ
የአዲስ አበባ ጅቡቲ የባቡር መስመር በዚህ በተያዘው መስከረም ወር መጨረሻ የሚመረቀው የባቡሩ መስመር ፕሮጀክት በወቅቱበሙከራ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ይኸው ከሶስት እስከ አምስት ወራት ይወስዳል የሚባለው የሙከራ ሂደት በሚጠናቀቅበት ጊዜ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።