1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአይሁዳዉያን ፀረ-ናዚ ትግል በፖላንድ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 16 2010

በዘር ጥላቻ እና በንቀት በነጮች የበላይነትም ላይ በተመሠረተው ርዕዮተ ዓለማቸው የጀርመን ናዚዎች አዉሮጳን ለመያዝ የዛሬ 80 ዓመት ገደማ ተነስተዋል። በተለይ አይሁዶችን እና የሌላ ሀገር የሚንቋቸዉን ዘሮች አንድ በአንድ እና ተራ በተራ እየለቃቀሙ በመርዝ እና በሰሩት በእሳት ምድጃቸው በያለበት እነሱን አቃጥለው ፈጅተዋል።

https://p.dw.com/p/2waWE
Polen 75. Jahrestag - Aufstand im Warschauer Ghetto Andrzej Duda
ምስል picture-alliance/dpa/C. Sokolowski

በዘር ጥላቻ እና በንቀት በነጮች የበላይነትም ላይ በተመሠረተው ርዕዮተ ዓለማቸው የጀርመን ናዚዎች አዉሮጳን ለመያዝ የዛሬ 80 ዓመት ገደማ ተነስተዋል። በተለይ አይሁዶችን እና የሌላ ሀገር የሚንቋቸዉን ዘሮች አንድ በአንድ እና ተራ በተራ እየለቃቀሙ በመርዝ እና በሰሩት በእሳት ምድጃቸው በያለበት እነሱን አቃጥለው ፈጅተዋል። ቁጥራቸውም ታሪክ ጸሐፊዎች እንደሚሉት በብዙ ሚሊዮን ይገመታል። ይህን የናዚዎች የአረመኔ ሥራም የአዉሮጳ አይሁዶች እንዴት ያለተቃዉሞ ዝም ብለው ተቀቡሉት፣ ለምንስ ተነስተው አልታሉትም ለሚለው የብዙዎች ጥያቄ በፖላንድ ዋና ከተማ በዋርሶው የዛሬ 75 ዓመት በአይሁዶች ጌቶ ውስጥ የተካሄደው አመፅ እንደምሳሌም እንደ መልስም ይጠቀሳል። በዕለቱ የአዉሮጳ እና ጀርመን መሰናዶ ይን ታሪክ አስመልክቶ የዶይቼ ቬለው ያን ፖላካት ከዋርሶው ያጠናቀረውን የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል አዘጋጅቶታል። 


ይልማ ኃይለ ሚካኤል 
ሸዋዬ ለገሠ