የአየር ንብረት ለዉጥ ተመልካች ጉባኤ በፓሪስ
ሰኞ፣ ኅዳር 20 2008ማስታወቂያ
በጉባኤዉ 150 ሃገራትን የሚወክሉ የሀገር መሪዎች፣ የአካባቢ ተፈጥሮ ጥበቃ ሚኒስትሮች፣ የአካባቢ ተፈጥሮ ጉዳይ ተመራማሪዎች እና ተሟጋቾች እንዲሁም በዘርፉ ላይ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ይሳተፋሉ። የዓለም የሙቀት መጠን ከሁለት ዲግሪ እንዳይበልጥ የሚለዉ የብዙዎቹ ሃገራት ሃሳብ ቢሆንም አፍሪቃ እና የደሴት ሃገራት ከሁለት ዲግሪ በታች ዝቅ እንዲል ነዉ የሚጠይቁት። የአየር ንብረት ለዉጥ እና የከባቢ አየር ብክለት ተጠቂ የሆኑ ሃገራት ከችግሩ ጋር ተላምደዉ ሊኖሩ እንዲችሉ ለብክለቱ ታሪካዊ ተጠያቂነት ያላቸዉ በኢንዱስትሪ የበለፀጉ ሃገራት ሊያዋጡት ቃል የገቡት የመቶ ሚሊየን ዶላር ጉዳይም ሌላዉ እልባት ያላገኘ አነጋጋሪ ጉዳይ ነዉ። ሸዋዬ ለገሠ ከፓሪሱ የአየር ንብረት ለዉጥ ተመልካች ጉባኤ ምን ይጠበቃል ስትል ኢትዮጵያዊ የአካባቢ ተፈጥሮ ተሟጋችን በአጭሩ አነጋግራለች።
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ