1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ ህብረት የአየር ንብረት ዲፕሎማሲ ቀን

ረቡዕ፣ ሰኔ 10 2007

።በዚሁ ውይይት ላይ ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት ባበቃው በቦኑ ዓለም ዓቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ በመጪዎቹ 15 ዓመታት የተቃጠለ የመርዛማ ጋዝ ብክለትን በሁለት ሶስተኛ ለመቀነስ የወሰደችው ጠንካራ አቋም በጥሩ ምሳሌነት ተነስቷል ።

https://p.dw.com/p/1Fihr
EU Klima-Gesprächsrunde in der deutschen Botschaft in Addis Abeba ACHTUNG SCHLECHTE QUALITÄT
ምስል DW/G. Tedla

[No title]

ሁለተኛው የአውሮፓ ህብረት የአየር ንብረት ዲፕሎማሲ ቀን ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ታሰበ ።እለቱን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የጀርመንና የብሪታኒያ ኤምባሲዎች አዘጋጅነት በጀርመን ኤምባሲ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ በተካሄደው ውይይት በዘርፉ የተሰማሩ መንግስታዊ ድርጅቶች ተወካዮች የልማት አጋሮች ምሁራን መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የግሉ ዘርፍ ተካፍለዋል ። በዚሁ ውይይት ላይ ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት ባበቃው በቦኑ ዓለም ዓቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ በመጪዎቹ 15 ዓመታት የተቃጠለ የመርዛማ ጋዝ ብክለትን በሁለት ሶስተኛ ለመቀነስ የወሰደችው ጠንካራ አቋም በጥሩ ምሳሌነት ተነስቷል ። ሃገሪቱ የአየር ብክለትን ለመቀነስ በኤኮኖሚ እንቅስቃሴዋ ተግባራዊ ያደረገችው የአረንጓዴ ፖሊሲ ፋይዳም በውይይቱ ተወስቷል ። ውይይቱን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ አለው ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ