የአውሮጳ ኅብረት ሶሪያና መካከለኛው ምሥራቅ
ማክሰኞ፣ ጥር 9 2009ማስታወቂያ
የአውሮጳ ኅብረት በጦርነት ለተመሰቃቀለችው ሶሪያ ፖለቲካዊ መፍትሄ የሚሻ ጉባኤ በመጪው ሚያዚያ ለማካሄድ ማቀዱን አስታወቀ ። የኅብረቱ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት ብራሰልስ ውስጥ ባካሄዱት ስብሰባ ላይ የኅብረቱ የውጭ ጉዳዮች ሃላፊ እንደተናገሩት ጉባኤው ከዚህ ቀደም በሶሪያ ሰብዓዊው ይዞታ እንዲሻሻል ቃል የተገባው እርዳታ ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በቅርብ ለመፈተሽ እንደሚረዳም አስታውቀዋል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በሶሪያ እና በመካከለኛው ምሥራቅ የሰላም ሂደት ላይ የተወያዩት የአውሮጳ ኅብረትን ጨምሮ 70 የሚደርሱ ሀገራት ዲፕሎማቶች ፓሪስ ውስጥ ባካሄዱት ስብሰባ እስራኤል እና ፍልስጤማውያን ቀጥተኛ የሰላም ንግግር እንዲጀምሩ ጥሪ ባቀረቡ ማግስት እንዲሁም የሶሪያ የሰላም ንግግር በካዛክስታን ዋና ከተማ አስታና ከመካሄዱ ከአንድ ሳምንት አስቀድሞ ነው። የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ዝርዝር ዘገባ አለው ።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ