1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ህብረት እና ስደተኞች

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 25 2009

ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ብዙ ስደተኞች በሜድትሬንያን ባህር በኩል ወደ አውሮጳ መግባት የያዙበት ድርጊት የአውሮጳ ህብረት ሀገራትን እያወዛገበ ይገኛል። ስደተኞችን የመቀበሉ ኃላፊነት በተለይ ስደተኞቹ መጀመሪያ በሚገቡባቸው ኢጣልያን በመሳሰሉ የደቡብ አውሮጳ ሀገራት ላይ አርፏል።

https://p.dw.com/p/2hVuQ
Frankreich Paris Migranten Flüchtlinge Camp Evakuierung
ምስል picture-alliance/AP Photo/T. Camus

የአውሮጳ ህብረት እና ስደተኞች

እነዚሁ የደቡብ አውሮጳ ሀገራት እና ህብረቱ ሌሎቹ የህብረቱ አባል ሀገራት ስደተኞችን በማስተናገዱ ተግባር ላይ እንዲተባበሩዋቸው ያቀረቡት ጥሪ ሰሚ አላገኘም። ስደተኞችን በመቀበሉ ጥያቄ ላይ በአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት መካከል የቀጠለው ልዩነት የአውሮጳ እና ጀርመን ዝግጅት ትኩረት ነው።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ