እርዳታ ለአስቸኳይ ጊዜ ትምሕርት
ሰኞ፣ ግንቦት 13 2010ማስታወቂያ
የአውሮጳ ሕብረት ግጭት እና የፖለቲካ ቀውስ ባሉባቸው አካባቢዎች የአስቸኳይ ጊዜ ትምሕርት መርሃ ግብሮችን ለማጠናከር እና ለማስፋት ማቀዱን አስታወቀ። የአውሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ባለፈው ዓርብ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ከመጪው የጎርጎሮሳዊው 2019 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ከሰብዓዊ እርዳታ ጠቅላላ በጀቱ 10 በመቶው ለአስቸኳይ ጊዜ ትምሕርት መርሃ ግብር እንዲውል ተወስኗል። ውሳኔው በተለይ ከአውሮጳ ሕብረት ውጭ በአስቸኳይ ሁኔታ ላይ የሚገኙትን እና የትምሕርት ዕድል የተነፈጋቸውን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕጻናትን ለመርዳት የሚያስችል ነው ተብሏል።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ