1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ሕብረት ከፍተኛ ባለሥልጣናት የካሌ ጉብኝት

ሰኞ፣ ነሐሴ 25 2007

የፈረንሳዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ማኑኤል ቫልስና የአዉሮጳ ሕብረት ከፍተኛ ባለስልጣናት በሰሜናዊ ፈረንሳይ ስደተኞች የሚገኙበትን አካባቢ ካሌን ዛሬ ጎበኙ።

https://p.dw.com/p/1GOjB
Frankreich Manuel Valls in Calais mit Timmermans und Avramopoulos
ምስል Getty Images/AFP/D. Charlet

[No title]


በፈረንሳይ ጠረፍ ከተማ የሆነችዉ ካሌን ከአፍጋኒስታን፤ ከሶርያ፤ ከኤርትራና፤ ከሱዳን የፈለሱ በሽዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች እንደሚገኙ ተመልክቶአል። አካባቢዉ ላይ የሚታየዉን የስደተኞች ችግር ለመቅረፍ የአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ለፈረንሳይ ሰባት ሚሊዮን ይሮ እንደሚሰጥም ተዘግቦአል። ፈረንሳይ በዚህ ዓመት ብቻ ወደ ስድሳ ሽ የሚሆኑ ስደተኞች እንደምትቀበል ሲጠበቅ፤ በአንፃሩ ጀርመን 800 ሽህ ስደተኞችን እንደምትቀበል ይጠበቃል። ዛሬ የፈረንሳዩ ጠቅላይ ሚኒስትርና የአዉሮጳ ከፍተኛ ባለስልጣናት የካሊስ ጉብኝት ላይ የተገኘችዉ የፓሪስዋ ወኪላችንን ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ከዝያዉ ከጉብኝቱ ቦታ አነጋግሪያት ነበር።

ሃይማኖት ጥሩነህን

አዜብ ታደሰ