1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ሕብረት መከላከያ ኃይል

ማክሰኞ፣ ኅዳር 5 2010

የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ግንኙነት ኃላፊ ወይዘሮ ፌዴሪካ ሞግሆረኒ እንዳስታወቁት አባል ሐገራት የጋራ የመከላከያ ኃይል እንዲመሰረት መስማማታቸዉ አንድነታቸዉን ለማጠናከር በእጅጉ የሚጠቅም ነዉ።

https://p.dw.com/p/2ncg5
Belgien EU beschließt Verteidigungsunion
ምስል Reuters

MMT (Beri.Brussel) EU-Africa Beziehungen - MP3-Stereo

የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት የመከላከያ ሚንስትሮች የሕብረቱ የጋራ መከላከያ ኃይል የሚመሠረትበትን ሠነድ ፈረሙ። ትናንት ብራስልስ ከተሰበሰቡ የመከላከያ ሚንስትሮች መካከል የ23ቱ ሐገራት ሚንስትሮች ሰነዱን ፈርመዋል። የተቀሩት የአራት ሐገራት ሚንስትሮችም በቅርቡ ይፈርማሉ ተብሏል። የሕብረቱ የዉጪ ግንኙነት ኃላፊ ወይዘሮ ፌዴሪካ ሞግሆረኒ እንዳስታወቁት አባል ሐገራት የጋራ የመከላከያ ኃይል እንዲመሰረት መስማማታቸዉ አንድነታቸዉን ለማጠናከር በእጅጉ የሚጠቅም ነዉ። የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ