የአዉሮጳ ሕብረት ለኤርትራ የልማት ርዳታ ሊሰጥ ነዉ
ዓርብ፣ መስከረም 7 2008ማስታወቂያ
ገንዘቡ ለኤርትራ የሚሰጠዉ በተለይ ከኤርትራ በገፍ የሚፈልሱትን ስደተኞች ለመግታት እንደሆነ የኮሚሽኑ የልማትና ዓለማቀፍ ትብብር ኃላፊ ኔቨን ሚኒካ ትናንት ናይሮቢ ኬንያ በሰጡት መግለጫ አስታዉቀዋል። ገንዘቡ በቀጥታ ሕዝቡ እጅ እንዲገባ እንደሚደረግም ባለስልጣኑ ተናግረዋል። የአዉሮጳ ሕብረት ፕሬዚዳንት ዦን ክሎድ ዩንከር ባለፈዉ ሳምንት ለሕብረቱ ፓርላማ ባደረጉት ንግግር ካለፈው ዓመት ከጥር ወር አንስቶ እስካሁን 500 ሺህ ስደተኞች ወደ አዉሮጳ መግባታቸዉን ገልጠዋል። ከነዚህም አብዛኛዎቹ ከሶርያ ሊቢያና ኤርትራ ነው የመጡት። ዝርዝሩን ገበያዉ ንጉሴ አዘጋጅቶታል ።
ገበያዉ ንጉሴ
አዜብ ታደሰ
ሒሩት መለሰ