የሜርክል በእጩነት የመቅረብ ፍላጎት እና አስተያየት
ዓርብ፣ ኅዳር 16 2009ማስታወቂያ
ይኸው የሜርክል ውሳኔ የሀገሪቱን የፖለቲካ ፓርቲዎችንም ሆነ የሀገሪቱን ዜጎች ብዙም አላስገረመም። ብዙ ጀርመናውያን የሜርክልን ዕጩነት በመደገፍ፣ ከርሳቸው የተሻለ ሌላ አማራጭ እንደሌለ እንደሚሰማቸው አስታውቀዋል። አንዳንዶች ደግሞ «ሴ ዴ ኡ»ን የመሩት የቀድሞው የጀርመን መራሒ መንግሥት ሄልሙት ኮል የገጠማቸውን ዓይነት ሽንፈት እንዳይደርስባቸው ስጋታቸውን ገልጸዋል። ሜርክል የሚወዳደሩበት የፖለቲካ መስክ በጣም በመከፋፈሉ፣ ከርሳቸው በፊት ለጀርመን አማራጭ፣ በምህፃሩ «አ ኤፍ ዴ» የተባለው የቀኝ አክራሪ ፓርቲ በፌዴራዊው ምክር ቤት፣ «ቡንድስታኽ» ለመጀመሪያ ጊዜ ብሔራዊ ውክልና ሊያገኝ የሚችልበት እድል መኖሩን ታዛቢዎች ይናገራሉ።
ይልማ ኃይለሚካኤል
አርያም ተክሌ
አዜብ ታደሰ