1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አቶ ነጋሽ ደራሲ እና ጸሐፌ-ተውኔትም ነበሩ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 11 2009

አንጋፋው ጋዜጠኛ አቶ ነጋሽ ገብረማርያም ትላንት ሐምሌ 10 ቀን 2009 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ የቀብር ሥነ-ስርዓታቸው ዛሬ ከሰዓት ተፈጽሟል፡፡

https://p.dw.com/p/2gkIw
Äthiopien Negash Gebre-Mariam Journalist
ምስል DW/G. Tedla

MMT_Ber. Addis Ababa (Veteran Journo Negash Gebremariam died on 93) - MP3-Stereo

አንጋፋው ጋዜጠኛ አቶ ነጋሽ ገብረማርያም ትላንት ሐምሌ 10 ቀን 2009 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ አቶ ነጋሽ “አዲስ ዘመን” ጋዜጣ  መታተም ከጀመረበት ጀምሮ ለሃያ ዓመት ያህል በዋና አዘጋጅነት ያገለገሉትን ብላታ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደዮሐንስን በመተካት ሁለተኛው የጋዜጣው አዘጋጅ በመሆን ሰርተዋል፡፡ የጋዜጠኝነት ትምህርታቸውን በአሜሪካ የተከታተሉት አቶ ነጋሽ የእንግሊዘኛው “ኢትዮጵያን ሄራልድ”ም አዘጋጅ ነበሩ፡፡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን በሥራ አስኪያጅነት መርተዋል፡፡ ከጋዜጠኝነት ሙያቸው ባሻገርም በድርሰት እና የተውኔት ስራዎቻቸውም ይታወሳሉ፡፡ የሁለት ልጆች አባት የነበሩት የአቶ ነጋሽ ገብረማርያም የቀብር ሥነ-ስርዓት ዛሬ ከሰዓት በሰዓሊተ ምህረት ማርያም ቤተ-ክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡ የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ በቅርብ ከሚያውቋቸው እና አብረዋቸው ከሰሩ ጋዜጠኞች ውስጥ  ላዕከማርያም ደምሴ እና ጸጋዬ ታደሰ በማነጋገር ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል፡፡   


ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ተስፋለም ወልደየስ

አዜብ ታደሰ