1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአቶ በቀለ የዋስትና ጉዳይ

ዓርብ፣ ሐምሌ 28 2009

የዋስትና መብት በ48 ሰዓታት ውሳኔ ማግኘት እንዳለበት ህጉ ቢያዝም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ተኛ ወንጀል ችሎት ይህን አለማድረጉ እና አሁንም ተጨማሪ ቀጠሮ መስጠቱ ቅር እንዳሰኛቸው ጠበቃቸው ለዶቼቬለ ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/2hh7S
Äthiopien Politiker Bekele Gerba
ምስል Addis Standard Magazine

የአቶ በቀለ ገርባ የዋስትና መብትጉዳይ

በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ በምህጻሩ ኦፌኮ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ-መንበር የአቶ በቀለ ገርባ የዋስትና መብት መጓተት ህጉን የሚፃረር እና መብታቸውንም የሚጥስ ነው ሲሉ ጠበቃቸው አማረሩ። የዋስትና መብት በ48 ሰዓታት ውሳኔ ማግኘት እንዳለበት ህጉ ቢያዝም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ተኛ ወንጀል ችሎት ይህን አለማድረጉ እና አሁንም ተጨማሪ ቀጠሮ መስጠቱ ቅር እንዳሰኛቸው ጠበቃቸው ለዶቼቬለ ገልጸዋል። በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቅ የነበረው ችሎቱ ተለዋች ቀጠሮ ሰጥቷል። ዝርዝሩን የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ