የአትሌት ታምሩ ደምሴ ተቃውሞ
ማክሰኞ፣ መስከረም 3 2009ማስታወቂያ
የተቃውሞ ምልክቱን በሜዳሊያ አሰጣጥ ስነ ስርዓቱ ላይም የደገመው ታምሩ ድርጊቱን ያደረገው የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰደ ያለውን የኃይል እርምጃ ለዓለም ህዝብ ለማሳየት እንደሆነ ይናገራል፡፡ ታምሩ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ እንደማይፈልግ እና ከዓለምአቀፉ ፓራኦሎምፒክ ኮሚቴ እገዳ ሊጣልበት እንደሆነ መስማቱን ለዶየቸ ቨለ ገልጿል፡፡ በእንግድነት ብቅ ያለው ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ከሌሊሳ ፈይሳ በኋላ በኦሎምፒክ መንደር በድጋሚ ተቃውሞውን ያሳየውን አትሌት ታምሩን አነጋግሮታል፡፡አትሌቱ በውድድሮች ላይ ስለነበረው ተሳትፎ በመግለጽ ይጀምራል።
ተስፋለም ወልደየስ
ነጋሽ መሐመድ