የአቡነ ጴጥሮስ ሐዉልት መመለስና የሕዝብ አስተያየት
ሰኞ፣ ጥር 30 2008ማስታወቂያ
ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም በፋሺስት ጣሊያን ወራሪዎች በጥይት ተደብድበዉ የተገደሉት የአቡነ ጴጥሮስ ሐዉልት፤ በመሬት ዉስጥ የሚያልፈዉን የአዲስ አበባን ቀላል የባቡር መጓጓዣ መስመር ግንባታ ሲባል ሚያዝያ 24 ቀን 2005 ዓ,ም ከቦታዉ መነሳቱ በወቅቱ ተገልጿል። የአዲስ አበባ ከተማዋ ነዋሪዎች ሐዉልቱ የተመለሰበትን ታሪካዊ ቦታ ለማየት አሁንም ወደ አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ እየሄዱ እንደሆነ ተሰምቶአል። ሐዉልቱ ወደ ነበረበት ቦታ መመለሱን አስመልክቶ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን አንዳንዶቹን በማነጋገር ዘገባ አዘጋጅቶልናል።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ