1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 15 2009

መንግሥት የደነገገዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የዉጭ ሃገራት ድፕሎማቶች «ከአዲስ አበባ ዙሪያ ከ40 ኪሎ ሜትር ዉጭ ሳያሳዉቁ እንዳይንቀሳቀሱ» ያሳስባል።

https://p.dw.com/p/2Rgvw
Äthiopien Tote bei Anti-Regierungs-Protesten in Bishoftu
ምስል DW/Y. Gegziabher

Emergency Declaration vs. Tourism Situation in Ethiopia - MP3-Stereo

በሌላ በኩል ቱሪስቶች ወይም አገር ጉብኚዎች ከቦታ ቦታ ለመዘዋወር ለማንም ማሳወቅ እንደሌለባቸዉ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ጽሕፈት ቤት ማስታወቁ ተዘግቧል። በአሁኑ ሰዓት በሀገሪቱ የጎብኚዎች ቁጥር ይሄን ያክል ነዉ ብሎ መናገር ያስቸግራል የሚሉት በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የህዝብና የዓለም አቀፍ ግኑኝነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቴር አቶ ገዛኸኝ አባቴ፣ በተለያዩ የቱሪስት መዳረሻ አካባቢዎች አሁን ካለዉ ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ከምጠበቀዉ በላይ ጎብኚዎች እየገቡ ነዉ ይላሉ። 

በአስጎብኚ  ሥራ ላይ ተሰማርተዉ የሚገኙ ነገር ግን ስማቸዉ እንዳይጠቀስና ድምፃቸዉም እንዳይቀረፅ የፈለጉ አንድ ግለሰብ፤ አዋጁ በቱሪዝም ኢንዱስትሪዉ ትልቅ ፍራቻ አንግሷል ካሉ በኋላ በፊት ሲደረጉ የነበሩ የጉብኝት ጉዞዎች፣ በተለይም ከሃይማኖታዊ ጉዞ ጋር የተያያዙት እንደነ አል ነጃሺ፤ አቡነ አረጋዊ እና ዝቋላ በመሳሰሉ አካባቢዎች፣ በከፍተኛ መጠን መቀነሱን ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።


ኢትዮጵያ ዉስጥ ባለዉ ያልተረጋጋ ሁኔታ ለዜጎቹ አስፈላጊዉን ድጋፍ ለማድረግ እንደማይችል የገለፀዉ በአዲስ አበባ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ፤ ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ ለሚሞክሩ አሜሪካዉያን የጉዞ ማስጠንቀቂያ አዉጥቷል። 


ይህ በሚመለከት በዶቼ ቬለ የፌስቡክ ገጽ ላይ ሰዎች እንድወያዩ አድርገን ነበር። አስተያየት ከሰጡን ዉስጥ የኢትዮጵያ መንግስት የሚለዉ «ዉሸት» ነዉ ምክንያቱም ሁለቱም ክልሎች፣ ኦሮሚያና አማራ፣ ባለመረጋጋት ዉስጥ ነዉ ያሉት ሲሉ፤ ሌሎች ደግሞ ይህ አዋጅ የቱሪዝም ኢንዱስትሪዉን በጣም ይጎዳል የሚል አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል። 

መርጋ ዮናስ

ሸዋዬ ለገሰ