1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአስቸኳይ አዋጁ መነሳቱና የተሰጠ አስተያየት

ረቡዕ፣ ግንቦት 29 2010

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማንሳት ባለፈዉ ቅዳሜ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበዉን ረቂቅ የዉሳኔ ሃሳብ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደዉ ሥብሰባ ማፅደቁን በርካታ ኢትዮጵያዉያን አወደሱ። 

https://p.dw.com/p/2yyxk
Flash-Galerie Der Blick aus meinem Fenster Addis Abeba Äthiopien
ምስል S. Mengist

« በጠ/ሚዉ ግፊትና የሰላም ትጋት አዋጁ ተነስቶአል» የሕዝብ አስተያየት

በሌላ በኩል የአዋጁን መነሳት የሚያበረታታ ቢሆንም፤ በሃገሪቱ ዘላቂ ሰላምና ሰላምና የዴሞክራሲ ነፃነት እንዲሰፍን መንግሥት የጀመረዉን ሥራ መቀጠል እዳለበት ተናግረዋል።

ለሁለተኛ ጊዜ የካቲት ወር አጋማሽ ለስድስት ወራት እንዲዘልቅ የታወጀዉ እና ዛሬ ሁለት ወራት ሲቀረዉ የተነሳዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ የሆነዉ «ከኮማንድ ፖስት አካላት እንዲሁም ከክልል የጸጥታ መዋቅሮች ጋር በተለያየ ወቅት ሰፊ ውይይት የተካሄደና ስምምነት ላይም በመደረሱ» መሆኑ ተገልፆአል። የአዋጁን መነሳት ኢትዮጵያዉያን ጥሩ ርምጃ ሲሉ አስተያየታቸዉን እየገለፁ ነዉ ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሽዋስ አሰፋ አዋጁ የታወጀበት ሁኔታ ትክክለኛ ባይሆንም መነሳቱ ጥሩ ርምጃ  ተናግረዋል።

መንግሥት ላይ ተቃዉሞ በመጠንከሩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መታወጁ እሙን ነዉ አሁንም  ደግሞ በጠቅላይ ሚንስትሩ ጥረት ተነሳ ሲሉ አቶ የሽዋስ አሰፋ ገልፀዋል።  

የአረና ትግራይ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አምዶም ገ/መድሕን በበኩላቸዉ ነፃነትን የገታዉ አዋጅ መነሳቱ ለፖለቲካዉ እንቅስቃሴ መሻሻል መልካም እድል ሲሉ ተናግረዋል።

እንድያም ሆኖ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ እያደረጉት ባሉት ሥራዎች በሃገሪቱ ሰላም ታየ እንጂ አዋጁ ሰላምን አላመጣም ሲሉም አክለዋል።  

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በመነሳቱ ደስተኞች ነን ግን ኢትዮጵያ ዘላቂ መፍትሄ ያስፈልጋታል ሲሉ የዶቼ ቬለ አድማጮች በድምፅ መልክት ልከዉልናል።

ሙሉ ቅንብሩን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።  

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ