የአሜሪካ ዕጩ ፕሬዝደንቶች ክርክር
ሐሙስ፣ ጥቅምት 10 2009ማስታወቂያ
ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ ከሁለት ሳምንታት በኋላ በሚደረገዉ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የሚፎካከሩት የተቀናቃኝ ፓርቲዎች ዕጩዎች ሰወሰተኛ እና የመጨረሻ የቴሌቪዥን ክርክር ትናንት ተደርጓል። የዲሞክራቲክዋ ፓርቲ ዕጩ ሒላሪ ክሊንተንና የሪፐብሊካን ተቀናቃኛቸዉ ዶናልድ ትራምፕ ትናንት ላስቬጋስ ከተማ ያደረጉት ክርክር በዉጪ ጉዳይ መርሕ፤ በስደተኞች ይዞታ እና በምጣኔ ሐብት ዕቅድ ላይ ያተኮረ ነበር። ትራምፕ ከብዙ ዓመታት በፊት ሴቶች በገንዘብና ዝና በቀላሉ ይማረካሉ ማለታቸዉ ከተጋለጠ ወዲሕ የደጋፊዎቻቸዉ ቁጥር እየቀነሰ ነዉ። የዋሽግተን ዲ ሲ ወኪላችን መክብብ ሸዋ የትናንቱን ክርክር ተከታትሎ የላከልን ዘገባ አለ።
መክብብ ሸዋ
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሰ