1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካ ብሔራዊ ፀጥታ ድርጅት ሚና በኢትዮጵያ

ሐሙስ፣ መስከረም 11 2010

የኢትዮጵያ መንግሥት ሽብርተኝነት በአፍሪቃ ቀንድ የደቀነውን ስጋት ለመታገል ዩኤስ አሜሪካ የሰጠችው የስለላ ቁሳቁስ እና ስልጠና ተቃዋሚዎቹን ለማፈኛ ተጠቅሞበታል ሲል አንድ ጽሁፍ አጋለጠ። ይህን ያለው ሰሞኑን የወጣ ያሜሪካውያን የድረ ገጽ ሕትመት ነው።

https://p.dw.com/p/2kU2H
NSA Symbolbild
ምስል picture-alliance/dpa

ኢትዮጵያ እና የኤንኤስኤ የስለላ ርዳታ

የአሜሪካ ብሔራዊ ፀጥታ ድርጅት፣ በምህፃሩ ኤንኤስኤ የሶማልያ ዓማፂ ቡድን አሸባብ ባካባቢው ያስፋፋውን ሽብር ለመታገል በሚል የስለላ ቁሳቁስ እና ስልጠና ለኢትዮጵያ መስጠቱን አንድ የሂውማን ራይትስ ዎች ተመራማሪ ቢያረጋግጥም፣ ይህ ጽሁፉ እንዳለው ተቃዋሚዎችን ለመጨቆኛ ተግባር መዋሉ ግን አሁንም አጠያያቂ መሆኑን ገልጿል።

መክብብ ሸዋ

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ