ማስታወቂያ
የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት ከፍተኛ ባለስልጣናትና ከ 13 ሃገራት የተዉጣጡ አፍሪቃ ሃገራት መንግሥታት ባለስልጥናት አዲስ አበባ ላይ የሁለት ቀናት ዉይይት አካሄዱ። የፍርድ ቤቱ አባላት አብዛኞቹ የአፍሪቃ ሃገራት መሆናቸዉ ይታወቃል።
የሰብዓዊ ጉዳዮች አያያዝ ላይ ለመምከር የጀርመንዋ መከላከያ ሚኒስቴር ኡርዙላ ፎን ደር ላይን በወግ አጥባቂ እስልምና መርህ የምትተዳደረዉን ስዑድ አረብያን ለመጀመርያ ጊዜ በመጎብኘት ላይ መሆናቸዉ ተገለጠ። በሃገሪቱ በያዝነዉ ዓመት ብቻ ከ 150 ሰዎች በላይ የግድያ ቅጣት ተፈጽሞባቸዋል።
በዓለማችን የሚገኙ ቀጭኔዎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን በመቀነሱ የመጥፋት ስጋት እንደተጋረጠባቸዉ የዓለም የተፈጥሮ ጥበቃ ማኅበር ገለፀ። በመረጃዉ መሰረት በዓለም ዙርያ ያሉት ቀጭኔዎች ቁጥር 100 ሺህ አይበልጥም።