1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ2010 ዓ.ም. የትንሳኤ በዓል ልዩ መሰናዶ

Eshete Bekeleእሑድ፣ መጋቢት 30 2010

የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር ከዋዜማው ጀምሮ ተዘዋውሮ እንዳስተዋለው የበዓል ገበያ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል፤ በጀርመኗ ፍራንክፈርት ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንስ የበዓል አከባበራቸውን ለዶይቼ ቬለ አጋርተዋል። አሜሪካ የሚኖሩት በበኩላቸው በሬ አርዶ ሥጋ የመከፋፈልን የቅርጫ ባሕል ይዘው ባሕር ተሻግረዋል።

https://p.dw.com/p/2vgef

የፋሲካ ገበያ እንዴት ዋለ? የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር ከዋዜማው ጀምሮ ተዘዋውሮ እንዳስተዋለው የበዓል ገበያ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል። በዘንድሮው የፋሲካ ገበያ አንድ በሬ ከ10 ሺህ እስከ 30 ሺህ ብር፤ ዶሮ ከ200 ብር እስከ 500 ብር መሸጡን የዮሐንስ ዘገባ ያስረዳል። እንዲህ ገበያ በተወደደበት ድህነት የተጫናቸው በዓሉን እንዴት ያከብሩ ይሆን? ዘጋቢያችን ልብስ በማጠብ የሚተዳደሩ አንዲት እናት አናግሯል። 

ሁለተኛው ዘገባችን የፋሲካ በዓል አከባበር በጀርመኗ የፍራንክፈርት ከተማ ምን እንደሚመስል ያስቃኘናል። እንዳልካቸው ፈቃደ ከሐይማኖት አባቶች እና ከከተማዋን ነዋሪዎች ጋር ቆይታ አድርጓል። 

እንዲህ ፋሲካን መሰል በዓል በኢትዮጵያ ሲከበር ገንዘብ አዋጥቶ፣ በሬ አርዶ፣ ሥጋ መከፋፈል የተለመደ ባህል ነው። ቅርጫ የመተጋገዝ፣ የአብሮነት መገለጫ ተደርጎ ይቆጠራል። በአሜሪካን ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ታድያ ይኸንኑ የቅርጫ ባህል ይዘው ባሕር ተሻግረዋል። መክብብ ሸዋ ይህንኑ የተመለከተ ዘገባ አለው።

ከአዲስ አበባ፣ ከፍራንክፈርት እና ከዋሽንግተን ዲሲ የተጠናቀረውን 2010 ዓ.ም. የትንሳኤ በዓል ልዩ መሰናዶን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

እንዳልካቸው ፈቃደ

መክብብ ሸዋ

እሸቴ በቀለ