የታንዛኒያ ምርጫ እና ዉዝግብ
ረቡዕ፣ ጥቅምት 17 2008ማስታወቂያ
ለፕሬዝደንትነት ከተፎካከሩት መካከል የገዢዉ ቻማ ቻ ማፒንዱዚ፤ በምህጻሩ CCM እጩ ሊያሸንፉ እንደሚችሉ ቢጠቆምም፤ የተቃዋሚዉ ወገን ተፎካካሪ ድምጽ እንደገና መቆጠር እንዳለበት እያሳሰቡ ነዉ። ራስገዟ ደሴት ዛንዚባር ደግሞ የተቃዋሚ ፓርቲዉ እጩ አሸንፈዋል ብሎ ፓርቲዉ ቢገልፅም፤ የታንዛኒያ የምርጫ ኮሚሽን የተባለዉን ዉጤት ሰርዟል። ከሁለቱም ወገን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስለድምጽ ቆጠራዉ መጭበርበር ሲናገሩ፤ ዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች አንዳንድ ችግሮች ታይተዋል ከማለት ዉጭ የእሁድ ዕለቱን የምርጫ ሂደት አወድሰዋል። ስለታንዛኒያ የምርጫ እና ዉዝግብ ናይሮቢ የሚገኘዉን ጋዜጠኛ ፋሲል ግርማን በስልክ ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ አነጋግሬዋለሁ።
ፋሲል ግርማ/ ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ