የቴርክ እና ሩሲያ አዲስ ግንኙነት
ሰኞ፣ ነሐሴ 9 2008ማስታወቂያ
ሩሲያ ቱርክ ላይ የኤኮኖሚ ማዕቀብ መጣሏ፤ አንካራን ብቻ ሳይሆን ራሷም ላይ ችግር ማስከተሉ አልቀረም። ዉላ አድራ ቱርክ ባለፈዉ ሰኔ ጀቱን ለመጣሏ ይቅርታ ሩሲያን ጠይቃለች። በቅርቡ በፕሬዝደንት ኤርዶኻን መንግሥት ላይ መፈንቅለ ስልጣን ሲሞከር ደግሞ ከሌሎች ሃገራት አስቀድማ ሞስኮ፤ ለቱርክ መንግሥት ሃዘኔታዋን ገለጸች። ይህም ሁለቱ ሃገራት በመካከላቸዉ የተፈጠረዉን መቃቃር አስወግዶ ዳግም ወደ አዲስ ግንኙነት እንዲሻገሩ አድርጓቸዋል። የዕለቱ ማኅደረ ዜና ይህን ይዳስሳል።
ገበያዉ ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ