1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተጠናከረው የወሮበላ ቡድኖች አመጽ በሄይቲ

ረቡዕ፣ የካቲት 27 2016

በሄይቲ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንሥትር አሪዬል ሔንሪን ለማስወገድ የዛቱ አመጸኛ ወንበዴዎች በዋና ከተማዪቱ ዛሬም ውጊያቸው አጠናክረዋል ። የወረበሎቹ ቡድን መሪ ጠቅላይ ሚንሥትሩን «እስከመጨረሻ ደም ጠብታችን እንፋለማለን» ሲሉ መዛታቸው ምናልባትም ሄይቲ ወደ ከፋ የእርስ በእርስ ጦርነት እንዳትገባ አስግቷል ።

https://p.dw.com/p/4dEiE

በሄይቲ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንሥትር አሪዬል ሔንሪን ለማስወገድ የዛቱ አመጸኛ ወንበዴዎች በዋና ከተማዪቱ ዛሬም ውጊያቸው አጠናክረዋል ። ትናንት ዋናውን የሀገሪቱን የአየር መንገድ ለመቆጣጠር ጥረት በማድረግ ተዋግተው ነበር ። ጠቅላይ ሚንሥትሩ ከሥልጣናቸው መውረድ የነበረባቸው ባለፈው ወር ነበር ።  የታጠቁ ወረበላ ቡድኖች ዋና ከተማዪቱ ፖርት ኦ ፕሪንስ ውስጥ በሚገኘው አየር መንገድ፤ እስር ቤቶች እና ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ የተቀናጀ ጥቃት ከፍተዋል ።

የወረበሎቹ ቡድን መሪ ጠቅላይ ሚንሥትሩን «እስከመጨረሻ ደም ጠብታችን እንፋለማለን» ሲሉ መዛታቸው ምናልባትም ሄይቲ ወደ ከፋ የእርስ በእርስ ጦርነት እንዳትገባ አስግቷል ። 

ሄይቲ ከ11 ሚሊዮን ትንሽ ከፍ ለሚል ነዋሪዋ 9,000 ግድም ፖሊሶች ብቻ ናቸው ያሏት ። ሄይቲ ሁከት ትርምሱን ለመቆጣጠር የተሳናትም ትመስላለች ።

ቪዲዮ ዘገባ፦ ዶይቸ ቬለ (DW) 
ምንጭ፦ አሶሺዬትድ ፕሬስ