1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተቃዋሚ ፓርቲዎችና የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ውይይት

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 9 2010

አራት የተቃዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የብሔራዊ መግባባት እና የሽግግር መንግሥት ምስረታ ስብሰባ በአዲስ አበባ የማድረግ እቅድ እንዳላቸው ገለጹ። እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ የሚንቀሳቀሱት መኢአድ፣ ኢራፓ፣ የሰማያዊ ፓርቲ እና የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ናቸው።

https://p.dw.com/p/2wCjX
Logo Äthiopien Opposition Partei AEUP

የብሔራዊ መግባባት ውይይት

አስተባባሪ ኮሚቴ መስርተው ስራ መጀመራቸውን ያስታወቁት የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ)፣ የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ(ኢራፓ)፣ የሰማያዊ ፓርቲ እና የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መሪዎች እንዳሉት፣ ስለዚሁ እቅዳቸው ከፕሬዚደንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ጋር በሰፊው ተወያይተው የፕሬዚደንቱን ድጋፍ አግኝተዋል። መሪዎቹ የስብሰባውን ጊዜ አልገለጹም።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ