1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዶናልድ ትራምፕ ውሳኔ የገና በዓል አከባበርን አቀዛቅዞታል።

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 16 2010

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ሊቃነ-ጳጳሳት ፍራንሲስ በዓመታዊ የገና በዓል ንግግራቸው የመፅሐፍ ቅዱሶቹን ዮሴፍ እና ማርያም ታሪክ ከወቅታዊው የስደት ቀውስ ጋር አነፃጽረውታል።

https://p.dw.com/p/2pw0g
Bethlehem Weihnachten Messe
ምስል Getty Images/H.Bader

የትራምፕ ውሳኔ በገና በዓል ላይ ጥላውን ጥሏል

በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የገና በዓል እየተከበረ ይገኛል። የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ሊቃነ-ጳጳሳት ፍራንሲስ በዓመታዊ የገና በዓል ንግግራቸው የመፅሐፍ ቅዱሶቹን ዮሴፍ እና ማርያም ታሪክ ከወቅታዊው የስደት ቀውስ ጋር አነፃጽረውታል። ሊቃነ-ጳጳሱ ዛሬ ስደተኞች እንደ ዮሴፍ እና ማርያም ሁሉ ከቀያቸው ለመነቀል መገደዳቸውን ተናግረዋል። ገንዘብ ለማካበት በኃይል በሕገ-ወጥ መንገድ ሰዎች የሚያዘዋውሩትንም አንስተው ገስጸዋል። 
የሕንድ የክርስትና እምነት ተከታዮች በወገናቸው በዓሉን በሥጋት ውስጥ ሆነው እያከበሩ ይገኛሉ። ወደ 24 ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑትን የዕምነቱን ተከታዮች ደኅንነት ለመጠበቅ የሕንድ መንግሥት የክልል መስተዳድሮች የጸጥታ ጥበቃቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቋል። ማድሕያ ፓራዴሽ በተባለው ግዛት ወግ አጥባቂ የሒንዱ እምነት ተከታዮች የካቶሊክ መነኮሳትን እና ቀሳውስትን መደባደባቸው የተሰማው በዚህ ወር መጀመሪያ ነበር። 
በፍልስጤም የክርስትና እምነት ተከታዮች በሕብረት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ውሳኔን ውድቅ አድርገዋል። የሐይማኖት መሪዎቹ ትራምፕ እየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ ነች ሲሉ የሰጡት እውቅና "አደገኛ" እና "ስድብ" ነው ብለዋል። በእየሩሳሌም የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ሊቀ-ጳጳስ አታላሕ ሐና እየሩሳሌም የተቀደሰች፣ መንፈሳዊ እና ብሔራዊ ቅርስ በሆነችው አድርገው ለሚቀበሉ የመላው ዓለም የእስልምና እና የክርስትና እምነት ተከታዮች አሜሪካ ያሳለፈችው ውሳኔ ጥቃት ነው ብለዋል። 
ለመሆኑ የገና በዓል አከባበር በቤተልሔም ምን ይመስል ይሆን? ዜናነሕ መኮንንን አነጋሬዋለሁ።