1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በበጀት ቅነሳው ኢትዮጵያ ትጎዳለች- የምጣኔ ሀብት ባለሙያ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 30 2010

አሜሪካ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምትመድበውን በጀት በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ መወሰኗ ድርጅቱ ለተለያዩ ሀገራት ለሚያደርገው ድጋፍ እጥረት ይገጥመዋል ተብሎ ተፈርቷል። የበጀት ቅነሳው ዳፋ ለኢትዮጵያም እንደሚተርፍ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

https://p.dw.com/p/2qWtn
Logo Vereinte Nationen UNO FLASH Galerie
ምስል un

በበጀት ቅነሳው ኢትዮጵያ ትጎዳለች- የምጣኔ ሀብት ባለሞያ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለተለያዩ ሀገራት የሚያደርገው ድጋፍ በበጀት እጥረት ምክንያት ሊቀንስ እንደሚችል እየተነገረ ነው። ለዚህ ደግሞ እንደ ዋንኛ ምክንያት እየተነሳ ያለው አሜሪካ ለመንግስታቱ ድርጅት የምትሰጠውን ድጋፍ በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ በመወሰኗ ነው። ዩናይትድ ስቴትስ ከሁለት ሳምንት በፊት ይፋ እንዳደረገችው ሀገሪቱ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለያዝነው የጎርጎሮሳዊው 2018 እና ቀጣዩ ዓመት ከምትመድበው በጀት 285 ሚሊዮን ዶላር ለመቀነስ ውሳኔ ላይ ደርሳለች። በዚህ ውሳኔ ኢትዮጵያ ተጎጂ እንደምትሆን አንድ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል። የዋሽንግተኑ ወኪላችን መክብብ ሸዋ ባለሙያውን አነጋግሮ ያጠናቀረውን ልኮልናል። 

መክብብ ሸዋ
ተስፋለም ወልደየስ
አርያም ተክሌ