1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ

ሐሙስ፣ ኅዳር 14 2010

በኢትዮጵያ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ዴቪድ ሺን ውሳኔው ተጨባጭ ማስረጃን ያገናዘበ አይደለም ብለዋል። የአካባቢውን መልክዐ ምድራዊ ፖለቲካ ያጠኑት ዶክተር ኢስማኤል ጎርሴ ደግሞ የፀጥታ ምክር ቤት አባላት ራሳቸው ውሳኔውን ምን ያህል ያከብሩታል የሚል ጥያቄ አንስተዋል።

https://p.dw.com/p/2o8cX
UN-Sicherheitsrat in New York | Thema Chemische Waffen in Syrien
ምስል Getty Images/AFP/T.A. Clary

«ውሳኔው ተጨባጭ ማስረጃን ያገናዘበ አይደለም»አምባሳደር ዴቪድ ሺን

 
የተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በኤርትራ ላይ ከዚህ ቀደም ጥሎ የነበረው የጦር መሣሪያ ማዕቀብ እንዲራዘም ማድረጉ አግባብ አይደለም ተባለ። ስለ ማዕቀቡ ዶይቼቬለ ያነጋገራቸው በኢትዮጵያ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ  አምባሳደር ዴቪድ ሺን ውሳኔው ተጨባጭ ማስረጃን ያገናዘበ አይደለም ብለዋል።ዶይቼቬለ ያነጋገራቸው  የአካባቢውን መልክዐ ምድራዊ ፖለቲካ ያጠኑት ዶክተር ኢስማኤል ጎርሴ በሰጡት አስተያየት የፀጥታ ምክር ቤት አባላት ራሳቸው ውሳኔውን ምን ያህል ያከብሩታል የሚል ጥያቄ አንስተዋል። ዝርዝሩን መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ ልኮልናል።   
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ