የብሪታንያው ልዑል ጋብቻ
ቅዳሜ፣ ግንቦት 11 2010ማስታወቂያ
የዛሬዎቹ ሙሽሮች የልዑል ሃሪ እና አሜሪካዊቷ ሜጋን ማርክል ጋብቻቸውን የፈጸሙበት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን በጎርጎሮሳውያኑ በ1528 ዓ.ም. የተመሰረተ ነው። ሰርጉ 2.7 ሚሊዮን ፓውንድ ያወጣ ሲሆን ወጪው በንግስት ኤልሳቤጥ የተፈሸነ ነው። የብሪታንያ መንግስት ለጸጥታ እና ጥበቃ 30 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ አውጥቷል። ይህ የግብር ከፋይ ገንዘብ ለዚህ ዝግጅት ብቻ መውጣቱ ያበሳጫቸው ብሪታንያውያን 30 ሺህ ፊርማ በማሰባሰብ ተቃውሟቸውን ለሀገሪቱ የተወካዩች ምክር ቤት አስገብተዋል።
እጅግ ዘመናዊ የንጉሳውያን ጋብቻ የታየበት የዛሬው የሰርግ ስነስርዓት ወግ አጥባቂውን ባህላዊውን የንጉሳውያን ቤተሰብ የሰርግ ስርዓት እምብዛም የተከተለ አልነበረም።
ማንኛውም የፖለቲካ ባለስልጣን ከተመረጡ 600 እንግዶች መካከል አልተካተተም። በመልካም ስራቸው ማህበረሰሰቡን የሚያገለግሉ 1200 ሰዎች፣ የበጎ ሰናይ ድርጅቶች ሰርጉን እንዲታደሙ ከተመረጡት መካከል ናቸው።
የብሪታንያው ልዑል ሃሪ የጋብቻ ስነርዓትን አስመልክቶ የለንደኗ ወኪላችን ሀና ደምሴ ያጠናቀረችውን ሙሉ ዘገባ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።
ሀና ደምሴ
ተስፋለም ወልደየስ