1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቢጫ ወባ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 11 2008

የዓለም የጤና ድርጅት እንደገለጸዉ በሽታዉ ነአንጎላ ዋና ከተማ ሉዋንዳ አስቀድሞ በመነሳቱ ወደ ኮንጎም እንዳይዛመት ለመከላከል ነዉ ክትባቱን የመስጠቱ ዘመቻ የተጀመረዉ።

https://p.dw.com/p/1Jjsn
Gelbfiebermücken
ምስል picture-alliance/dpa/A. Weigel

[No title]

የዓለም የጤና ድርጅት መንግሥታዊ ካልሆኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በተለያዩ የአፍሪቃ ሃገራት የቢጫ ወባ ክትባት ዘመቻ ጀመረ። በዛሬዉ ዕለት በዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ ድንበር የለሽ ሃኪሞች፤ ሕፃናት አድን እና ሌሎች በርካታ ድርጅቶች ከሀገሪቱ መንግሥት ጋር በመሆን 10,5 ሚሊየን የሚገመቱ ሰዎችን እስከ ቀጣይ አስር ቀናት ድረስ ለመከተብ ተሠማርተዋል። ክትባቱን በአንጎላ እና ኮንጎ ድንበር አካባቢም መስጠት ተጀምሯል። የዓለም የጤና ድርጅት እንደገለጸዉ በሽታዉ ነአንጎላ ዋና ከተማ ሉዋንዳ አስቀድሞ በመነሳቱ ወደ ኮንጎም እንዳይዛመት ለመከላከል ነዉ ክትባቱን የመስጠቱ ዘመቻ የተጀመረዉ። በዚህ ዘመቻም ከ 40 ሚሊየን በላይ ሕዝብ እንደሚከተብ ይጠበቃል።

ፀሐይ ጫኔ

ሸዋዬ ለገሠ