ቢል ጌትስ በአዲስ አበባ
ዓርብ፣ ሐምሌ 15 2008ማስታወቂያ
በተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራቸው የሚታወቁት የማይክሮሶፍት ባለቤት ቢል ጌትስ አዲስ አበባ ውስጥ ለሃገር ውስጥ እና ለውጭ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በሃገሪቱ ለአረንጓዴ የግብርና ዘዴ ተጨማሪ ድጋፍ ቢሰጥ ፈታኝ ችግሮችን መቋቋም እንደሚቻልም ተናግረዋል ። ርሳቸው እና ባለቤታቸው የመሠረቱት ቢልና ሜሊንዳ ጌትስ የተባለው ድርጅታቸው በኢትዮጵያ ከ500 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ካፒታል የሚያንቀሳቀሱ ከ150 የሚበልጡ ፕሮጀክቶች እንዳሉት የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል ።ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ