የሽብርተኝነት ተፅዕኖ በፈረንሳይ ኤኮኖሚ ላይ
ረቡዕ፣ ኅዳር 8 2008ማስታወቂያ
በፈረንሳይ የሚኖረው ሐዝብ ሰላማዊ ኑሮ መምራት ይፈልጋል። ሀገሪቱን በመጎብኘት ላይ ያለዉ ቱሪስትም ሆነ በከተማዋ የሚዘዋወረዉ ሰላማዊ ሕዝብ ፀጥታዉን ይሻል። ከትንሹ ነጋዴ እስከ ትልቁ የንግድ ኩባንያ ባለቤት የሆነዉ ነጋዴም ቢሆን ንግዱ የሰመረ፣ የድካሙን ዋጋ በፀጥታ እና ደሕንነቱ በተጠበቀ መንገድ መሰብሰብን ይሻል። በዚህ መኃል ግን ሽብር ፈጣሪዎች ሳይታሰብ የሽብር ጥቃትን ሲጣል ግን የከተማዋ ጎብኝ ቱሪስቱም ሆነ ነዋሪዉ ኑሮዉ ሥራዉ ደሕንነቱ ሁሉ ይዘበራረቃል። ነጋዴዉም ቢሆን የሥራዉና የኑሮው መሠረት ይናጋል ይዳከማል። በዓመት ከሰማንያ ሚሊዮን ሰው በላይ የሚጎበኛት ፈረንሳይ በተለይ ከተማዋ ፓሪስ አሁን ያጋጠማት ችግርም ይኸው ነዉ። የቱሪዝሙ ዘርፍ በፈረንሳይ ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢ ላይ የያዘው ድርሻ በቀላሉ የሚገመት አይደለም። የፈረንሣይ አየር መንገድ ኤር ፍራንስ እና አኮርር የሚባለው የብዙ ሆቴሎች ባለንብረትእንዳረጋገጡት፣ በቅርቡ በተፈጠረው አደጋ -በጥቂት ቀናት ጊዜ ውስጥ ብቻ፣ የአክሲዮናቸው ዋጋ አሁን በጉልህ ቀንሶዋል።
አንድርያስ ቤከር / ይልማ ኃይለሚካኤል
አዜብ ታደሰ