1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሽብር ጥቃት ሥጋትና ዓለም አቀፉ ፀረ-ሽብር ርምጃ

እሑድ፣ ታኅሣሥ 10 2008

የዛሬ 14 ዓመት በዩናይትድ ስቴትስ ከደረሰዉ የአሸባሪዎች ጥቃት ወዲህ ዓለም ከቀን ወደ ቀን በሽብር ሥጋት ዉስጥ ትገኛለች። የሽብር ጥቃቱን አፀፋ ለመመለስ፤ ብሎም አሸባሪን ከምድረ-ገጽ ለማጥፍት በሜል፤ አሜሪካና አጋሮችዋ በተለያዩ አገራት ዘመቻ ከፍተዉ ነበር።

https://p.dw.com/p/1HQeb
Weltkugel Globus Afrika
ምስል picture alliance / dpa

የሽብር ጥቃት ሥጋትና ዓለም አቀፉ ፀረ- ሽብር ርምጃ

ይሁንና የሽብሩን ጥቃት ለመከላከል የሚወሰደዉ ፀረ-ሽብር ርምጃ ሙሉ በሙሉ ዉጤታማ አለመሆኑ ነዉ የሚታየዉና የሚነገረዉ። ጥቃትና የአፀፋ ጥቃቱ ቀጥሎ፤ አሸባሪዎቹም ሳይጠፉ ስማቸዉን በመቀያየር የፀረ ሽብሩ ዘመቻም መቋጫ ሳያገኝ እንደዉም ፅንፈኝነት እየገነነ አገር እየወደመ፤ ሽብሩ አሜሪካ፤ አፍሪቃ፤ መካከለኛዉ ምስራቅ ብሎ መኃል አዉሮጳ ደርሷል። በሌላ በኩል የፀረ- ሽብሩን ዘመቻ ተከትሎ የተለያዩ መንግሥታት የፀረ-ሽብር አዋጅን አዉጥተዉ የሰብዓዊ መብትን፤ የመናገርና የፕሬስ ነፃነትን፤ እንደሚደፈጥጡ ይህንኑ ርምጃቸዉንም አጠናክረዉ መቀጠላቸዉ በየጊዜዉ አቤት የሚሉት የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት መግለጫ የአደባባይ ምሥጢር ነዉ። ይህ እንወያይ መሰናዶ የዓለማችን የሽብር ጥቃት ሥጋትና ዓለም አቀፉን የፀረ-ሽብር ርምጃ ይቃኛል። ዉይይቱ በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግሥት የአዲስ አበባና የኦሮምያ ልዩ ዞን የተቀናጀ እቅድን በመቃወም በተፈጠረው ግጭት እጃቸው አለበት በተባሉትና በአሸባሪነት በተፈረጁት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ ማስጠንቀቁን በተመለከተም ተወያዮች የሰጡት አስተያየት ተካቶበታል።

ሙሉዉን ዉይይት የድምፅ ማድመጫዉን ማዕቀፍ በመጫን ይከታተሉ።

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ