የሺሞን ፔሬስ ህልፈተ ሕይወት
ረቡዕ፣ መስከረም 18 2009ማስታወቂያ
እጎአ ከ2007 እስከ 2014 ዓም ፕሬዚደንት የነበሩት የሰራተኛው ፓርቲ መሪ ፔሬስ ሁለት ጊዜ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው አገልግለዋል። እስራኤል እና የእስራኤል ሕዝብ፤ የእስራኤል መስራች አባት በሚባሉት በቀድሞው ፕሬዚደንት ሺሞን ፔሬስ ሞት ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶታል። የተለያዩ የውጭ ሀገራት መሪዎችም የሀዘን መግለጫቻውን ለእስራኤል መንግ/ስት እና ሕዝብ በመላክ ላይ ናቸው። ሺሞን ፔሬስ እጎአ በ1994 ዓም ከቀድሞው የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ይትዝሀቅ ራቢን እና የቀድሞው የፍልስጤማውያን መሪ ያሲር አራፋት ጋር ባንድነት በፍልስጤማውያን እና በእስራኤል መካከል በኦስሎ፣ ኖርዌይ ለደረሱት የሰላም ስምምነት የኖቤል ሰላም ተሸላሚ ሆነዋል።
ዜናነህ መኮንን
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ