1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሊያ እና የአረብ ኤሚሬቶች ዉዝግብ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 9 2010

የሶማሊያ መንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች ባለፈዉ ሳምንት ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የተላከ አስር ሚሊዮን የሚጠጋ ዶላር ከያዙ ወዲሕ የሁለቱ ሐገራት ዉዝግብ እየተካረረ ነዉ። የሞቃዲሾ መንግሥት ለጦር ሠራዊቱ ማሰልጠኛ ከአቡዳቢ ይደረግለት የነበረዉን ርዳታ እና ድጋፍ በሙሉ አቋርጧል።

https://p.dw.com/p/2wCGN
Somalia Mogadischu | Flughafen-Areal
ሞቃዲሾ አየር ማረፊያ አካባቢምስል DW/S. Petersmann

ሶማሊያ እና የተ.አረብ ኤሚሬቶች ግንኙነታቸውን አቋረጡ።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በበኩሏ ከሶማሊያ መንግሥት ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጥዋን ትናንት አስታዉቃለች። የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት የሁለቱ መንግሥታት ጠብ የፋርስ ባሕረ ሰላጤ ቀዉስ፤ የየመኑ ጦርነት እና የዱባዩ የወደብ ድርጅት የበርበራ ወደብን መኮናተሩ ያስከተለዉ መዘዝ ነዉ።

ቻላቸዉ ታደሰ

ነጋሽ መሀመድ