የስፖርት ጥንቅር _ ጥቅምት አንድ፣ 2008 ዓም
ሰኞ፣ ጥቅምት 1 2008ማስታወቂያ
በቻይና በተካሄደው የወንዶች የሜዳ ቴኒስ ውድድር ሰርቢያዊው ኖቫክ ዶኮቪች፣ በሴቶች ደግሞ ስጳኛዊቱ ጋርቢን ሙጉሩዛ አሸናፊዎች ሆነዋል። በሶቺ፣ ሩስያ መኪና እሽቅድድም ብሪታንያዊው ልዊስ ሀሚልተን በማሸነፍ ነጥቡን ወደ 302 ከፍ አድርጓል። ጀርመን፣ ፖላንድ ፣ አልባንያ እና ሩሜንያ ፈረንሳይ እአአ በ2016 ዓም ለምታስተናግደው የአውሮጳ ዋንጫ ማጣሪያ ግጥሚያ አልፈዋል።
ሃና ደምሴ
አርያም ተክሌ