1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስደተኞች ችግርና መጻኢ ዕድል በሊቢያ

ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 14 2009

አብዛኛዎቹ ሕይወታቸው በሜድትራኒያን ባሕር የሚያልፈው ስደተኞች መነሻቸው ሊቢያ ነው። ሊቢያ በአህኑ ወቅት ማዕከላዊ መንግስት የሌላትና ሕግና ሥርዓት አልባም አገር ናት።

https://p.dw.com/p/2bjw1
Bootsflüchtlinge im Mittelmeer
ምስል picture alliance/dpa/S.Palacios

ትኩረት በአፍሪቃ

አብዛኛዎቹ ሕይወታቸው በሜድትራኒያን ባህር የሚያልፈው ስደተኞች መነሻቸው ሊቢያ ነው። ሊቢያ በአኹኑ ወቅት ማዕከላዊ መንግስት የሌላትና ሕግና ሥርዓትም የሌለባት አገር ናት። በመሆኑም ወደ አውሮፓ ለመሻገር አልመው በተለይ ከሰሀራ በታች ከሚገኙ አገሮች ተነስተው  ሊቢያ የሚገቡ ስደተኖች ለከፋ ችግር የሚጋለጡባት ምድር ኾናለች። በታጣቂ ሚሊሻዎች ወይንም በሕገወጥ የሰው አዘዋዋሪ ነጋዴዎች እጅ ወድቀው ሕይወታቸው የሚያልፈው የስደተኞች ቁጥርም ቀላል እንዳልሆነ ነው የሚገመተው። የአውሮጳ ኅብረት የስደተኞች ፖሊሲ፣ ስደተኞቹ ለሚያጋጥማቸው ችግር አስተዋጾ እያደረገ እንደሆነ ነው የስደትኞች መብት ተከራካሪ  ድርጅቶች የሚናገሩት።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ