1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሳልህ ሞት የሰላም ተስፋዉን ጨልሞታል፤

ረቡዕ፣ ኅዳር 27 2010

በየመን ሁቲ ሚሊሺያዎች የቀድሞዉ የሀገሪቱ መሪ አሊ አብደላ ሳልህ መገደል ከሳዉድ አረቢያ እና ተባባሪዎቿ ጋር ሊደረግ የነበረዉ የሰላም መቀራረብ ተስፋ እንደቀበረዉ የፒለቲካ ተንታኞች እየገለፁ ነዉ።

https://p.dw.com/p/2osb3
Jemen Ali Abdullah Saleh und König Abdullah bin Abd al-Aziz
ምስል picture alliance/AP Photo/A. Nabil

«የሳልህ ሞት የሰላም ተስፋዉን ቀብሮታል፤»

በካይሮ የሰንዓ ማዕከል የስልት ጥናት ዳይሬክተር ለፈረንሳይ የዜና ወኪል እንደገለፁት፤ መሠረት የነበሩት ሳልህ ወደማይመለሱበት ስለሄዱ የየመን የፖለቲካ መፃኢ ዕድል አሁን ፍፁም ተቀይሯል። ባለፈዉ ቅዳሜ ነበር ጠንካራዉ የየመን ፖለቲከኛ ከሁቲ አማፅያን ጋር ለሦስት ዓመት የነበራቸዉን መቀራረብ ወደጎን ብለዉ፤ የተኩስ አቁም እና የተዘጉ መተላለፊያዎች ይከፈቱ ዘንድ «ጠላት» ከሚሏት ሳዉዲ ጋር አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር ዝግጁነታቸዉን ይፋ ያደረጉት። በእርግጥም የእሳቸዉ መገደል የመን ዉስጥ የተጫረዉን እሳት የሚያግመዉ እንጂ የሚያጠፋዉ እንደማይሆን የሳዉዲ የፖለቲካ ተንታኞችም እያረጋገጡት እንደሆነ ነዉ ሪያድ የሚገኘዉ ወኪላችን ስለሺ ሽብሩም የገለፀልን። ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ስለሺ ሽብሩ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ