የሰማያዊ ፓርቲ ጋዜጣዊ መግለጫ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 11 2009ማስታወቂያ
“እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ዋናው ሥራችን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አላማዎችን ለህዝቡ ማስተዋወቅ መሆን ሲገባው ስራችን እስረኛ መጠየቅ እና ስንቅ ማመላለስ ሆኗል” ብለዋል የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ፡፡ ሁኔታው የከፋው ደግሞ በአማራ ክልል መሆኑን ጠቅሰዋል። “በሀገሪቱ በተለይ በአማራ ክልል የሰማያዊ አባላትን ማሰር እና መዋከብ በከፋ ሁኔታ ቀጥሏል፡፡ ይህንን ከሁለት ወር በፊት ለአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ጥያቄ አቅርበን ነበር፡፡ መልሰን አላገኝም፡፡ ትላንትና ባህርዳር ያሉ አባሎቻችን እና አመራሮች ፍርድ ቤት ቀርበው ነበረ። ክሱንም አይተነዋል፡፡ የክስ ይዘት የለውም፡፡ ነሐሴ አንድ ቀን 2008 ዓ.ም ባህር ዳር ከተማ በነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት ሰማያዊ ጠርቶ ነበር፣ ህዝብ ራሱ ነው የጠራው በሚል ውዝግብ በዚያ ምክንያት ወደ 20 አባላት ነው የታሰሩት።፡ ባህር ዳር ከተማ ውስጥ ሁሉንም በሚባል መልኩ መዋቅሩን አፍርሰውታል” ብለዋል አቶ የሺዋስ።፡
ዮሃንስ ገብረእግዚያብሔር
ተስፋለም ወልደየስ
አዜብ ታደሰ