1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

Merga Yonas Bula
ሰኞ፣ የካቲት 13 2009

ከተቋቋመ አምስት ዓመት የሆነው የሰማያዊ ፓርቲ የአመራር የሊቀመንበርነት ቦታ የይገባኛል ዉዝግብ ዉዝግብ ዉስጥ ይገኛል። አራት ወር በፊት ፓርቲዉ አረደገ በተባለዉ ጠቅላላ ጉባኤ አቶ የሺዋስን የፓርቲዉ ሊቀመንበር አድርጎ መርጧዋል።

https://p.dw.com/p/2XwA0
Äthiopien Wahlen 2015
ምስል DW/E. Bekele

Blue Party Leadership Crisis - MP3-Stereo

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጉዳዩን ሲከታተል ከቆየ እና  የምርጫ ሒደትን ከመረመረ በኋላ፣ ምርጫውን በሕጉና በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት መፈጸማቸውን በማረጋገጥ መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም. የተደረገው ጠቅላላ ጉባዔ ፣ በቦርዱ ተቀባይነት ያገኘ መሆኑን ባለፈው የካቲት 8 ቀን 2009 ዓ.ም ወስኗል።  

ቦርዱ በዚህ  ዉሳኔ ላይ መድረስ የቻለዉ በምን መስፈርት ነዉ? በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝብ ግንኝነት ሃለፊ  አቶ ተስፋለም አባይ ፓርቲዉ ያደረገዉን ጠቅላላ ጉባኤ ባለዉ ሕግና የፓርቲዉ ደንብ ተከትሎ ነዉ ይላሉ።

ቦርዱ ዉሳኔዉ ላይ መድረስ የቻለዉ የፓርቲዉን የምርጫ ሕደትን መርምሮ መሆኑን አቶ ተስፋለም ብናገሩም የፓርትዉ የምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ስሌሺ ፈይሳ ግን ጠቅላላ ጉባዔው የተደረገው የሚፈለገዉ ኮረም ያሟላ አይደለም ስሉ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።

የፓርቲዉን ሊቀመንበር ለመምረጥ የተደረገዉ ጉባኤ የሚፈለገዉ ያህል ሰዎች እንደተገኙና ከሌሎች ተቃዋም ፓርት ተወካዮች እንደነበሩ አቶ የሺዋስ አሰፋ በበኩላቸዉ ተናግረዋል።

ሰማያዊ ፓርቲ ከተቋቋመ አምስት ዓመት ማስቆጠሩን የሚናገሩት አቶ የሺዋስ የነበረዉን የፓርቲዉ አቋምና አሰራር እንደምያስቀጥሉም ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።

የቦርዱን ዉሳኑኔ እንዴት ይመለከቱታል ብለን በዶይቼ ቬሌ የፌስቡክ ደህረ ገፅ ላይ አድማጮቻችንን አወያይተን ነበር። «በጣም ያሳዝናል» ያሉት አንድ አስተያየት ሰጭ «መጀመሪያ ራሳችውን መምራት ሳትችሉ ነው አገር እንምራ የምትሉት» ስሉ የጠየቁት ስኖሩ፣ ሌሎች ደግሞ «ይህ ውሳኔ የምርጫ ባርድ ሳይሆን የራሱ የወያኔ ድርጊት ነው፣ ምክንያቱም ለነሱ የህዝብ ድጋፍ ያለው ፓርቲ ስጋት መስሎ ስለሚታያቸው» ስሉ አስተያየታቸዉን ሰንዝረዋል።

መርጋ ዮናስ

አርያም ተክሌ