የሩሲያ እና የኢትዮጵያ ስምምነት
ዓርብ፣ የካቲት 30 2010ማስታወቂያ
ሩሲያ ለኤሌክትሪክ ማመንጫ የሚረዳ የኑክሌር ጣቢያ ለኢትዮጵያ ለመገንባት ተስማማች።ዛሬ አዲስ አበባን የጎበኙት የሩሲያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ባደረጉት ዉይይት ከአዲስ አበባ በቀጥታ ወደ ሞስኮ የአዉሮፕላን በረራ እንዲደረግም ተስማምተዋል።የሁለቱ ሐገራት ባለሥልጣናት በሌሎች ምጣኔ ሐብታዊ እና የንግድ ግንኙነቶች ላይም ተስማምተዋል።የሩሲያዉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር አዲስ አበባ የገቡት የአሜሪካዉ አቻቸዉ የአዲስ አበባ ጉብኝታቸዉን እንዳጠናቀቁ ነዉ።ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ