ሰኞ፣ ሰኔ 26 2009
ማስታወቂያ
በ2003 (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ነዉ) የኢራቅን ሕዝብ «ነፃ ለማዉጣት» ሐብታሚቱን አረባዊት ሐገር ላይ የወረዉ ጦር ዛሬም እዚያዉ ይዋጋል።የዓለም ብቸኛ ልዕለ ኃያል ሐገር መሪ ዶናልድ ትራምፕ ግን ጋዜጠኞችን ለመስደብ ይባትላሉ።አዉሮጶች የአረብ-አፍሪቃ ስደተኛ እንዳይመጣባቸዉ ድንበራቸዉን የሚዘጉ፤ የአፍሪቃ አንባገነኖችን በዩሮ የሚገዙበትን ብልሐት ያዉጠነጥናሉ።የዓረብ ቱጃር፤ኃያል፤ትላልቅ መንግስታት ባንድ አድመዉ አረባዊቷን ትንሽ ሐገርን ይቀጣሉ።ሶሪያዎች የዓለም ዘመናዊ ጦር መሳሪያ ይፈተሽባቸዋል።ኢራቆች በተለይ ሞሱሎች ዛሬም ያልቃሉ አስራ-አራተኛ ዓመታቸዉ።እስከመቼ? ላፍታ አብረን እንጠይቅ።