1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

  የምናንጋግዋ በዓለ ሲመት

ዓርብ፣ ኅዳር 15 2010

ምናንጋግዋ ለበዓለ ሲመታቸዉ ለተሰበሰበዉ ሕዝብ እንደነገሩት መሬታቸዉ ተወርሶ ለሌሎች ለተሰጠባቸዉ ሰዎች አዲሱ መንግስታቸዉ ካሳ ይከፍላል። በመጪዉ የጎርጎሪያዉያን 2018 ሊደረግ የታቀደዉ ምርጫም በተያዘለት ጊዜ ይደረጋል።

https://p.dw.com/p/2oCjR
Simbabwe Harare Vereidigung Präsident Emmerson Mnangagwa
ምስል picture-alliance/AP Photo/B. Curtis

(Q&A) Mnangagwa-Vereidigung - MP3-Stereo

የቀድሞዉ የዚምባብዌ ምክትል ፕሬዝደንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ዛሬ ቃለ መሐላ ፈፅመዉ የፕሬዝደትነቱን ሥልጣን በይፋ ያዙ። ምናንጋግዋ ለበዓለ ሲመታቸዉ ለተሰበሰበዉ ሕዝብ እንደነገሩት መሬታቸዉ ተወርሶ ለሌሎች ለተሰጠባቸዉ ሰዎች አዲሱ መንግስታቸዉ ካሳ ይከፍላል። በመጪዉ የጎርጎሪያዉያን 2018 ሊደረግ የታቀደዉ ምርጫም በተያዘለት ጊዜ ይደረጋል። ምናንጋግዋ የፕሬዝደንትነቱን ሥልጣን የያዙት የቀድሞዉ የዚምባብዌ ፕሬዝደንት ሮበርት ሙጋቤን የሐገሪቱ የጦር ጄኔራሎች በቁም ካሰሯቸዉ በኋላ ሥልጣን በመልቀቃቸዉ ነዉ። በዓለ ሲመቱን እና የአዲሱ ፕሬዝደንትን መልዕክት በተመለከተ የጁሐንስበርግ ወኪላችን መላኩ አየለን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
መላኩ አየለ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ