1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ምርጫ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 4 2010

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በፃፈዉ ደብዳቤ ግን ዘንድሮ ምርጫ ለማድረግ አስተማማኝ ፀጥታ ባለመኖሩ የምርጫዉ ጊዜ በአንድ አመት እንዲራዘም ጠይቋል።ምክር ቤቱም የቦርዱን ጥያቄ ተቀብሎ ምርጫዉ በ2011 እንዲደረግ በአብላጫ ድምፅ ወስኗል።

https://p.dw.com/p/2vwch
Äthiopien Wahlen 2015
ምስል DW/E. Bekele

(Beri.AA) AA & DD Council elections postponed - MP3-Stereo

የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ መስተዳድሮች የምክር ቤት አባላት ምርጫ በአንድ ዓመት እንዲራዘም የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወሰነ።የሁለቱ ምክር ቤቶች እና የፌደራሉ ምክር ቤት  የማሟያ ምርጫ በቅርቡ ይደረጋል ተብሎ ነበር።ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በፃፈዉ ደብዳቤ ግን ዘንድሮ ምርጫ ለማድረግ አስተማማኝ ፀጥታ ባለመኖሩ የምርጫዉ ጊዜ በአንድ አመት እንዲራዘም ጠይቋል።ምክር ቤቱም የቦርዱን ጥያቄ ተቀብሎ ምርጫዉ በ2011 እንዲደረግ በአብላጫ ድምፅ ወስኗል።በስልጣን ላይ ያሉት የሁለቱ ከተሞች አስተዳደር ዘመነ ሥልጣን ዘንድሮ ሥለሚያበቃ የከተሞቹን የአስተዳደሪነት ሥልጣን  የሚረከበዉ ወገን ማንነት ግን በዉል አልታወቀም።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ