1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ የምሁራን ዉይይት እና በፖለቲካዉ ያላቸዉ ሚና

እሑድ፣ መስከረም 22 2009

በቅርቡ ኢትዮጵያ ዉስጥ የተካሄደዉ የምሁራን ዉይይት እና ምሁራን በሀገሪቱ በፖለቲካ ያላቸዉ ሚና

https://p.dw.com/p/2QnYu
Hauptcampus der Universität Addis Abeba AAU
ምስል DW

በኢትዮጵያ የምሁራን ዉይይት እና በፖለቲካዉ ያላቸዉ ሚና

በ1940ዎቹ በቀዳማዊ  ኃይለ ሥላሴ የተቋቋመዉ ዩኒቨርሲቲ ለሀገሪቱ የምሁራን መፍለቂያ ብቻ ሳይሆን የለዉል አቀንቃኖች የተገኙበት እንደሆነ ይነገርለታል። ለዚህም የያኔ ነገሥታቱም ሆኑ ከዚያ ወዲህ በትረ ስልጣን የጨበጡ መሪዎች ዓይናቸዉን እንደጣሉበት የሚናገሩ አሉ። የሀገሪቱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ቁጥሩ እንደጨምሩ ማድረጉን የሚገልጸዉ ስልጣን ላይ ያለዉ መንግሥት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ትምህርት ከመጀመሩ አስቀድሞ የዩኒቨርሲቲዉን ማኅበረሰብ እየሰበሰ ዉይይት ያካሂዳል። ዉይይቱ ስለትምህርት ጥራት ነዉ ይባል እንጂ፤ በተግባር የሚቀርበዉ ኢህአዴግ አሳካኋቸዉ ያላቸዉ ድሎች ዝርዝር፤ በመሆኑ በዚህ ዓመት ስብሰባዉን እንደታሰበዉ እንዳይከናወን እንዳደረገዉ መምህራን ይናገራሉ። በዝምታ መሸበባቸዉ የሚነገርላቸዉ ምሁራን በዚህ ወቅት በ2008 በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተቀሰቀሰዉ አለመረጋጋት፤ የጠፋዉ የሰዉ ሕይወት፣ እንዲሁም የሚፈጸመዉ እስራትና እንግልት፤ ቆም ብሎ ሊታሰብበት እንደሚገባ አመላክተዋል። ሙሉ ዉይይቱን ከድምጽ ዘገባዉ ይከታተሉ!

ሸዋዬ ለገሠ   

ልደት አበበ