የሜርክል መልካም ምኞት
ሐሙስ፣ መጋቢት 27 2010ማስታወቂያ
አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያን ቀውስ ይወጣሉ ከሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ጋር ፖለቲካዊ ውይይት ያካሂዳሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል አስታወቁ ። ሜርክል ለዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት ሀገሪቱ የተጋረጡባትን ከባድ ፈተናዎችን ማለፉ እንዲሳካላቸው ተመኝተዋል። ለረዥም ጊዜ የዘለቀው የሁለቱ ሀገራት የቅርብ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ፍላጎታቸው መሆኑን ያሳወቁት ሜርክል በደስታ መግለጫቸው መንግሥታቸው ለብልጽግና እና ለተጨማሪ ነጻነት ጉዞ ላይ የምትገኘውን ኢትዮጵያን ይደግፋል ብለዋል።
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ