ኮሚቴው ለኢትዮጵያ ለውጥ ድጋፉን ገልጿል።
ሐሙስ፣ ሰኔ 14 2010ማስታወቂያ
የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የአመራር አባላት ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ኮሚቴው ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ስለላከው ደብዳቤ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አቡበከር አሕመድ ዛሬ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ እንዳሉት ኮሚቴው አምስት ዋና ዋና ነጥቦችን ያካተተ ደብዳቤ ነው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የላከው። ይዘቱም ከዚህ ቀደም የቀረቡት የሙስሊሙ ህብረተሰብ ጥያቄዎች እንዲመለሱ የሚጠይቅ እና በኢትዮጵያ ለተጀመረው ለውጥ ድጋፍ እንደሚሰጥ የሚገልጽ መሆኑንም ተናግረዋል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ