1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመድረክ ጉባኤ እና የድርድር ጉዳይ

ሰኞ፣ ግንቦት 27 2010

ገዢው ፓርቲ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር በሚያካሂደው ውይይት ለመሳተፍ በቅድሚያ መስተካከል አለባቸው በሚል ካስቀመጣቸው ጉዳዮች አንዱ መመለሱን የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ገለጸ።

https://p.dw.com/p/2yvCZ
Professor Beyene Petros derzeitiger Vorsitzender des Oppositionsbündnisses Medrek
ምስል DW

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳቱ አስፈላጊ ነው፤

መድረክ ከመንግሥት ጋር ለመወያየት በሀገሪቱ ላይ የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ ላቀረበው ጥያቄ ፈጣን ምላሽ ማግኘቱን የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር እና የውች ግንኙነት ኃላፊው ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ለዶይቸ ቬለ አመልክተዋል። በመጪዉ ምርጫ የመሳተፉ ጥያቄ መድረክ በድርድሩ ውስጥ ከገባ በኋላ እንደሚመዝነውም ገልጸዋል። መድረክ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል።


ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጎስ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ